የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድ ክለቡን እንዲያሻሽሉ አርሰናል ለሚኬል አርቴታ የሰጠውን ጊዜ ያህል እንደማይሰጣቸው ገልጸዋል።

“ሁለቱ ክለቦች የተለያዩ ናቸው” ያሉት ሩበን አሞሪም ስራቸው አርቴታ በአርሰናል ገጥሞት ከነበረው ፈተና ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ሲጠየቁ “እንደዛ አይሰማኝም” ብለዋል።

ነገርግን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ፈተናውን ያለፉበት መንገድ እንደ ትልቅ ማነሳሻ ተደርጎ የሚታይ ነው ሲሉ ሩበን አሞሪም ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

አርሰናል የተለየ ክለብ እንደሆነ ይሰማኛል ሲሉ የገለፁት አሰልጣኙ “ነገርግን ማንችስተር ዩናይትድ አርቴታ የተሰጠውን ያህል ጊዜ አይሰጠኝም” ሲሉ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here