13.6 C
London
Saturday, August 2, 2025

ራያን ቼርኪ: “ባሎን ዶር ማሸነፍ እችላለሁ”

የማንቸስተር ሲቲ አዲስ ፈራሚ ፈረንሳዊው ራያን ቼርኪ፣ በቀጣይ የባሎን ዶር ሽልማትን የማሸነፍ ህልም እንዳለው ገልጿል። ተጫዋቹ ማንቸስተር ሲቲን ለመቀላቀል የመረጠውም ይህን የባሎን ዶር ህልሙን ለማሳካት በማሰብ እንደሆነ ተናግሯል።

የ21 ዓመቱ ራያን ቼርኪ በ36.5 ሚሊዮን ዩሮ ዝውውር ወደ ማንቸስተር ሲቲ ፊርማውን ማኖሩ አይዘነጋም። “ሮድሪ ባሎን ዶር ሲያሸንፍ የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ሆኖ ማሳካት የሚቻል እንደሆነ አይተናል” ያለው ቼርኪ፣ “እዚህ ያለሁት ለዚህ ነው” ሲል አክሏል።

ራያን ቼርኪ ዛሬ በአሜሪካ የሚገኘውን የማንቸስተር ሲቲ ስብስብ ልምምድ ተቀላቅሏል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here