ስፔናዊው የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጫዋች ኒኮ ዊሊያምስ በዚህ ክረምት ባርሴሎናን ለመቀላቀል እንደሚፈልግ ተገልጿል። ተጫዋቹ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ለሚፈልጉት ክለቦች ያሳወቀ ሲሆን፣ ክለቦቹም ይህን መረጃ ማግኘታቸው ተዘግቧል።
ዊሊያምስ ባርሴሎናን መቀላቀል ህልሙ እንደሆነ የገለጸ ሲሆን፣ የዝውውሩ መሳካት በባርሴሎና እጅ መሆኑ ተነግሯል። ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም አርሰናል እና ባየር ሙኒክ ፍላጎት እንዳላቸው ይታወቃል።