በክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር ባየር ሙኒክ የኒውዚላንዱን ክለብ ኦክላንድ ሲቲን 10 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በዚህ ጨዋታ ጀማል ሙሲያላ ሀትሪክ ሲሰራ፣ ቀሪዎቹን የባየር ሙኒክ ግቦች ኦሊሴ (2)፣ ኮማን (2)፣ ቶማስ ሙለር (2) እና በይ አስቆጥረዋል። ሁለት ግቦችን በማስቆጠር እና አንድ አመቻችቶ በማቀበል ኦሊሴ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል።
ይህ ድል ባየር ሙኒክ በአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ታሪክ በበርካታ የግብ ልዩነት ያሸነፈበት ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል።
የቀጣይ መርሃ ግብር:
- ባየር ሙኒክ ቅዳሜ ከቦካ ጁኒየር ጋር ይጫወታል።
- ኦክላንድ ሲቲ አርብ ከቤኔፊካ ጋር ይጫወታል።