የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን (ፒኤስጂ) ፈረንሳዊ ተከላካይ ሉካስ ሄርናንዴዝ፣ በዚህ ዓመት እንደ ኡስማን ዴምቤሌ ጥሩ ዓመት ያሳለፈ ተጫዋች እንደሌለ ገልጿል።
ሄርናንዴዝ አስተያየቱን ሲሰጥ “በግል አፈፃፀም የዴምቤሌን ያህል ጥሩ ዓመት ያሳለፈ ተጫዋች የለም። ባሎን ዶር ይገባዋል” ብሏል። አክሎም “ዴምቤሌ በየትኛውም መንገድ አስደናቂ ዓመት አሳልፏል። ድምፃቸውን ለእሱ እንደሚሰጡ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲል ሉካስ ሄርናንዴዝ ተናግሯል።