የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጃክ ግሪሊሽ ከሰሞኑ የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ መታየቱ ችግር እንደማይሆንባቸው ገልጸዋል።

ጃክ ግሪሊሽ ከቀናት በፊት ከኤፌ ካፕ ጨዋታ በኋላ በተለያዩ ምሽት ቤቶች ተዘዋውሮ የአልኮል መጠጥ ሲጠጣ መስተዋሉ ሲዘገብ ነበር።

በተጨማሪ በምሽት ቤቱ ለነበሩ ተጠቃሚዎች ሙሉ የመጠጥ ሒሳብ ክፍሎ መውጣቱ ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ፔፕ ጋርዲዮላ “ተጨዋቾቼን የምለካው ሜዳ ላይ እና ልምምድ ላይ ምን ሰሩ በሚለው ነው” ብለዋል።

አክለውም “ሁሉም ተጨዋቾች የግል ህይወት አላቸው ማድረግ የሚፈልጉትን ያድርጉ” ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here