የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከነገው ጨዋታ በፊት ተቃውሞ ለማሰማት ቀጠሮ ከያዙ የክለቡ ደጋፊዎች ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።
የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ከነገው የአርሰናል ጨዋታ በፊት ከፍተኛ ተቃውሞ ለማሰማት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መግለፃቸው አይዘነጋም።
ደጋፊዎቹ የክለቡ ባለቤቶች ላይ ለሚያሰሙት ተቃውሞ ሁሉም ሰው ጥቁር ለብሶ እንዲመጣ ጥሪም አቅርበዋል።
“ክለቡ ውስጥ ላለ ሁሉም ሰው ከባድ ጊዜ ነው እኔ እና ተጨዋቾቹ ማድረግ የምንችለው ብቸኛው ነገር ማሸነፍ ነው” ሲሉ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።
አክለውም “ሁሉም ሰው የመቃወም መብት አለው፤ ይህንን ማድረግ ጥሩ ነገር ይመስለኛል ሁሉም ሰው ድምፅ አለው” ሲሉ ገልጸዋል።