የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበን ሁለት ወጣት ተጨዋቾቹን ለፕርሚየር ሊጉ ክለብ ቼልሲ መሸጡን በይፋ አስታውቋል።
ሰማያዊዎቹ ጂዮቫኒ ኩዌንዳ እና ዳርዮ ኢሱጎን ከስፖርቲንግ ሊስበን 74 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት ማስፈረማቸው ተገልጿል።
የ 17ዓመቱ ተስፈኛ ጂዮቫኒ ኩዌንዳ 52 ሚልዮን ዩሮ ሲወጣበት በ 2026 ሰማያዊዎቹን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።
22 ሚልዮን ዩሮ ወጥቶበት ሰማያዊዎቹን የተቀላቀለው ዳርዮ ኢሱጎ በበኩሉ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ችልሲን ይቀላቀላል።