19.3 C
London
Saturday, August 2, 2025

የዚህን ጀግና አስደናቂ የእግር ኳስ አነሳስ እዩልኝማ…

የዚህን ጀግና አስደናቂ የእግር ኳስ አነሳስ እዩልኝማ…

ፌስቡክ ላይ ቪዲዮዎችን ሳሳልፍ አንድ የብስራት ስፖርት ቪዲዮ ጋ ደረስኩ እና ቀልቤን ገዛው ፡ ስለዚህ ልጅ አነሳስ እና የደረሰበት ቦታ በቀላሉ እንዳልተገኘ የሚገልጽ። ብታነቡት ይመረጣል!

ከምንም ተነስቶ እዚህ መድረስ የቻለ የበርካቶቹ የሀገራችን እግር ኳስ ተጫዋቾች ምሳሌ የሆነ ወጣት ተጫዋች።

#መሐመድ_አበራ ይባላል የሀላባ ልጅ ነው ፤ በመቻል እግር ኳስ የሙከራ ዕድል አግኘቶ መሳፈርያ ያጣል እናም ጓደኛው እንጀራ ከምጥሸጥ እናቱ ሰርቆ 500 ብር ይሰጠዋል እርሱም በቃጥራ ተሳፍሮ ለ 3:00 ሙከራ ሌሊት 11:00 አዲስ አበባ ይገባል።

የሙከራ ሰአቱ እስኪደርስ ከነትጥቁ ስቴድየም ጊቢ ውስጥ ገብቶ ይተኛና ሰአቱ ሲደርስ የመጀመርያ ሙከራ ያደርግና ወደቀጣዩ ዙር በማለፍ ለ 2ተኛ ዙር ከ 3ት ቀን በኃላ ተመልሶ እንዲመጣ ይነገረዋል።

እጁ ላይ ያለው ገንዘብ ወደ ሀላባ መመለስ ስለማይችል ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ይገባዋል። ከኃላም ከሙከራው ከሚመለሱ የአዲስ አበባ ልጆች ጋር ወደ መስቀል አደባባይ ሔዶ ቁጭ ይላል።

እናም መሸት ሲል የጎዳና ተዳዳሪዎች ያገኙት እና ” ምን ሆነህ ነው?  ” ብለው ይጠይቁታል ፤ እርሱም ስለሁሉም ነገር ነገራቸው እና ከነሱ ጋር 3ት ቀን መቆየት እምደሚችል ይነግሩት እና ከነሱ ጋር ምግብ እና መኝታ እየተጋራ መቆየት እንደሚችል ይገልጹለት እና አብሯቸው ይቆያል።

በ 3ተኛው ቀንም ወደ መቻል ስፖርት ክለብ ለሙከራ ሲሔድ ከተጫዋቾች መሐል የአሁኑ የመቻል ዋናው ቡድን ረዳት አሰልጣኝ እርሱን ለብቻ በመጥራት ሌሎች ጭምር ከእርሱ ላይ ስልኩን ተቀብለው መመረጥ ከለመመረጣቸውን እንዲያረጋግጡ ጭምር ይገልጽላቸዋል።

ሰበታ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ለገጣፎ እና በአሁኑ ሰአት በሊጉ መሪ ኢት.መድህን እየተጫወተ ይገኛል! ለብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ ጥሪ ተደርጎለት በአለም ዋንጫ ማጣርያ ስብስብ ውስጥ መካተተም ችሎ በአሁኑ ሰአት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ይገኛል።

ይህን ሁሉ አልፎ ዛሬ ላይ ለደረሰበት ደረጃ መድረስ መቻል በራሱ ትልቅ ጥረት ፣ ባህሪ እና ጽናት ይጠይቃል። ለበርካቶቹ ተስፋ እንዳትቆርጡ መማርያ የሚሆን ወጣት ተጫዋች ነው።

✉️ Bediru (XV)

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here