“ፊፋ ለሜሲ የአለም ዋንጫ ሰጥቶታል” ኤቭራ። የቀድሞ ፈረንሳዊ የኋላ መስመር ተጫዋች ፓትሪስ ኤቭራ ፊፋ የ2022 አለም ዋንጫን ለአርጀንቲና አሳልፎ ሰጥቷል ሲል ተችቷል። አርጀንቲና በ2022 ኳታር አለም ዋንጫ ውድድር ፈረንሳይን በመለያ ምት አሸንፋ ሻምፒዮን መሆኗ የሚታወስ ነው።
“በ2022 ዓለም ዋንጫውን ለሜሲ እንደሰጡት ሁላችንም እናውቃለን” ያለው ኤቭራ ሁሉም ነገር አስቀድሞ የተፃፈ ነበር ሲል ገልጿል። በወቅቱ ፈረንሳዊያን እንኳን ሊዮኔል ሜሲ ዋንጫውን እንዲያሸንፍ ይፈልጉ ነበር ሲል ኤቭራ አስተያየቱን ሰጥቷል።