አስደናቂው አርጀንቲናዊ የፊት መስመር ተጫዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ ማንችስተር ዩናይትድን ሊለቅ እንደሚችል ታዋቂው የስፖርት ሚዲያ “The Athletic” ዘግቧል። ማንችስተር ዩናይትድ ለተጫዋቹ የሚቀርበውን የዝውውር ገንዘብ አጥንቶ ከወሰነ ጋርናቾ ክለቡን እንደሚለቅ ተጠቁሟል። ከዚህም በተጨማሪ ዴንማርካዊው አጥቂ ራስሙስ ሆይሉንድም ቡድኑን ሊለቅ ከሚችሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ተነግሯል።
በተቃራኒው ግን ወጣቱ እንግሊዛዊ አማካይ ኮቢ ማይኖ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በኦልድትራፎርድ የመቆየት እድሉ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።