19.3 C
London
Saturday, August 2, 2025

“ዴብሮይን እንዲለቅ አንፈልግም” ሲልቫ

“ዴብሮይን እንዲለቅ አንፈልግም” ሲልቫ

የዜናው ዘገባ:

የማንችስተር ሲቲው ድንቅ አማካይ በርናርዶ ሲልቫ የቡድን አጋሩ ኬቨን ዴ ብሮይን መሰናበት በቡድናቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።

በርናርዶ ሲልቫ በሰጠው አስተያየት “የቡድኑ የተወሰነ መንፈስ ከዴብሮይን ጋር አብሮ ይሄዳል። የእሱ መልቀቅ በእውነትም ያሳዝናል” ብሏል። አክሎም “ዴብሮይን እንዲሄድ በፍጹም አንፈልግም” ሲል በምሬት ተናግሯል።

ሲልቫ አክሎም “ለእኔ ኬቨን ዴ ብሮይን በማንችስተር ሲቲ ታሪክ ውስጥ ምርጡ ተጫዋች ነው” ሲል የእሱን ታላቅነት መስክሯል።

ይህ አስተያየት የወጣው ቤልጂየማዊው ኮከብ ኬቨን ዴ ብሮይን በዚህ የውድድር ዓመት መጨረሻ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን ኮንትራት እንደማያድስ ይፋ ካደረገ በኋላ ነው።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here