17.6 C
London
Saturday, June 14, 2025

“አርሰናልን መደገፍ ትግል ነው ግን እወደዋለሁ” ሼዝኒ

የባርሴሎናው ግብ ጠባቂ ሼዝኒ በዚህ የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አርሰናልን እንደማይደግፍ በግልጽ ተናግሯል።

ሼዝኒ ስለ ቀድሞ ክለቡ ሲናገር “የአርሰናል ደጋፊ መሆን የማያባራ ትግል ነው፤ ነገር ግን ያንን እወደዋለሁ። ጥሩ ነገሮችን እያሳዩ ነው፣ ጨዋታቸውን ለመመልከት እጥራለሁ፣ የክለቡ እብድ ደጋፊ ነኝ” ብሏል።

ሆኖም አክሎም “በእያንዳንዱ ጨዋታ ድጋፍ አደርጋለሁ። በዚህ ዓመት በሻምፒየንስ ሊግ ግን ትልቅ ደጋፊያቸው አይደለሁም፤ ምክንያቱም አንድ የምደግፈው ክለብ አለኝ” ሲል አሁን ለሚጫወትለት ክለብ ያለውን ታማኝነት አሳይቷል።

በመጨረሻም ሼዝኒ “አርሰናል በዚህ ዓመት ሻምፒየንስ ሊጉን እንደማያሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት አስተያየቱን አጠናቋል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here