የሌስተር ሲቲው ታሪካዊ የፊት መስመር አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ለክለቡ ላደረገው ታላቅ አስተዋፅኦ ክብር ለመስጠት ሀውልት ሊሰራለት መሆኑ ተገለጸ።
በዚህ የውድድር ዓመት መጨረሻ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ከሌስተር ሲቲ ጋር ለመለያየት የተዘጋጀው የ38 ዓመቱ አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ሀውልቱ ከሌስተር ሲቲው ኪንግ ፓወር ስታዲየም ውጭ እንደሚቆም ንግግሮች እየተደረጉ ናቸው።
በተጨማሪም በታቀደው ሀውልት ላይ ጄሚ ቫርዲ በእጁ ላይ ያለውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አርማ እየጠቆመ እንደሚታይ ተነግሯል። ይህም ቫርዲ ክለቡን ወደ ታላቅ ስኬት ማለትም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያመራበትን ታሪካዊ ወቅት የሚያሳይ ይሆናል።
ጄሚ ቫርዲ ለሌስተር ሲቲ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን በ496 ጨዋታዎች ለክለቡ አስደናቂ 198 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።