የፈረንሳይ ሊግ ሻምፒዮንነቱን ቀደም ሲል ያረጋገጠው ፓሪስ ሴንት ዠርሜን (ፒኤስጂ) በዚህ የውድድር ዓመት የመጀመሪያውን ሽንፈት ዛሬ ምሽት አስተናግዷል።
ፒኤስጂ በሜዳው ኒስን ያስተናገደበት ጨዋታ በ1-3 ውጤት በኒስ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ አስደናቂ የ30 የሊግ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ካደረገ በኋላ ይህን ሽንፈት አስተናግዷል። ክለቡ ሊጉን ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ በማጠናቀቅ ልዩ ታሪክ ለመጻፍ ሶስት ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውት ነበር።
በተቃራኒው ኒስ ለአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ጠቃሚ ሶስት ነጥቦችን ማሳካት ችሏል።
ፒኤስጂ በቀጣይ መርሃ ግብሩ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።