19.3 C
London
Saturday, August 2, 2025

“በአርሰናል ጨዋታ ደጋፊውን ለመካስ ሁሉንም እናደርጋለን” ኤንሪኬ

የፓሪስ ሴንት ዠርሜን (ፒኤስጂ) ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው በሚቀጥለው ሳምንት ከእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ጋር በሚያደርጉት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገው ደጋፊዎቻቸውን ለማስደሰት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ትላንት ምሽት በሜዳቸው ኒስን 1-3 በሆነ ውጤት የተሸነፉበትን ጨዋታ አስመልክተው አስተያየታቸውን የሰጡት ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው በዚያ ጨዋታ 30 የግብ እድሎችን መፍጠሩን አስታውሰዋል። አክለውም “ከአርሰናል ጋር በሚደረገው ጨዋታም እንደ ትላንቱ አይነት የጨዋታ እንቅስቃሴ ማሳየት እንፈልጋለን” ብለዋል።

በተጨማሪም “በአርሰናል ጨዋታ የተሰበረውን የደጋፊዎቻችንን ልብ ለመመለስ እና እነሱን ለማስደሰት የምንችለውን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን” ሲሉ አሰልጣኝ ኤንሪኬ አረጋግጠዋል።

ፒኤስጂ በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ምሽት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ከእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ጋር እጅግ ተጠባቂ ፍልሚያ የሚያደርግ ይሆናል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here