የቼልሲው ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው የኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫን በማንሳት “ተመልሰናል” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።
ማሬስካ በሰጡት አስተያየት “በዚህ አመት የኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ቼልሲ በድጋሚ ወደ ቀድሞ ክብሩ መመለሱን በግልፅ ያሳያል” ብለዋል። አክለውም “ቼልሲ እስካሁን ያላሸነፈው ብቸኛው የአውሮፓ ዋንጫ የኮንፈረንስ ሊግ ነው። ይህንን ዋንጫ የምናሸንፍ ከሆነ ደግሞ ሁሉንም የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒዮና ዋንጫዎችን ያነሳ የመጀመሪያው ክለብ እንሆናለን” ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።