የኖርዌዩ ክለብ ቦዶ ግሊምት ተጫዋቾች ከመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኋላ በሀገራቸው ለሚሰራጭ ጋዜጣ ቶተንሀምን “ደካማ ቡድን ነው” በማለት መተቸታቸው ተዘግቧል።
የክለቡ ተከላካይ ፍሬድሪክ ሾቮልድ “ቶተንሀም የሚፈጥረው ጫና በቀላሉ የሚቆም ነው፤ ተጫዋቾቻቸው በቀላሉ ይወድቃሉ። በአጠቃላይ ከኖርዌይ ሊግ ቡድኖች የተሻሉ አይደሉም” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
ሌላው የቡድኑ ተጫዋች አንድሬ ጆርካን በበኩሉ “የተሸነፍነው በቡድኑ ጫና ሳይሆን በተለየ የቶተንሀም ተጫዋቾች የግል ጥረት ነው” ብሏል።
ይህን አስተያየት የሰሙት የቶተንሀም አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በሰጡት ምላሽ “በጣም ጥሩ። ዛሬ ምሽት ስታዲየሙ ሁሉንም ነገር ይናገራል” በማለት በሜዳ ላይ ለሚሰነዘረው ትችት ምላሽ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።