የእግር ኳስ ፀሐፊዎች ማህበር ለ2024/25 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማን እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጫዋች መሐመድ ሳላህ የእግር ኳስ ፀሐፊዎች ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
ሳላህ በዚህ ሽልማት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛውን ድምጽ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
ለሽልማቱ ድምጽ ከሰጡ ጋዜጠኞች መካከል 90 በመቶ ያህሉ መሐመድ ሳላህን እንደመረጡ ተገልጿል።
መሐመድ ሳላህ የእግር ኳስ ፀሐፊዎች ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ለሶስተኛ ጊዜ በማሸነፍ ልዩ ስኬት አስመዝግቧል።
የእግር ኳስ ፀሐፊዎች ማህበር ከየትኛውም የእንግሊዝ ክለብ ይልቅ ለሊቨርፑል ተጫዋቾች አስራ ስድስት ጊዜ ይህን ሽልማት ሰጥቷል።