የሊቨርፑሉ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ ክለቡን ለመልቀቅ በወሰነው ውሳኔ በጣም ማዘናቸውን ተናገሩ።
አርኔ ስሎት በሰጡት አስተያየት “አርኖልድ ለመልቀቅ በመወሰኑ በሊቨርፑል ውስጥ እንዳለ ሁሉም ሰው እኔም እጅግ በጣም ተበሳጭቻለሁ” ብለዋል።
አክለውም “ያዘንኩት አንድ ምርጥ ሰው ክለቡን ስለሚለቅ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የጎን ተከላካዮች አንዱ በመልቀቁ ጭምር ነው” ሲሉ አርኖልድን ምን ያህል እንደሚያጡት ገልጸዋል።
ሆኖም “አንድ ጥሩ ተጫዋች ሲሄድ ሌላ ጥሩ ተጫዋች ይመጣል” በማለት ለወደፊቱ የተሻለ ተስፋ እንዳላቸው አመልክተዋል።
በተጨማሪም አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በእሁድ ከሚደረገው የአርሰናል ጨዋታ ጋር በተያያዘ አርኖልድ በመጠባበቂያ ወንበር ላይ እንደሚቀመጥና ኮኖር ብራድሌይ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ እንደሚሰለፍ አረጋግጠዋል።
“ብራድሌይ በአርሰናል ጨዋታ በቋሚነት ይጀምራል ምክንያቱም ለቀጣዩ አመት ዝግጅት እንዲያደርግ ጨዋታ ያስፈልገዋል፤ በእሱ ላይ ትልቅ እምነት አለን” ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።