የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን የማረጋገጥ ጉዳይ በራሳቸው እጅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ጋርዲዮላ በሰጡት አስተያየት “ሶስት ጨዋታዎችን ካሸነፍን በቀጥታ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር እናመራለን፤ ሁሉም ነገር በእኛ ቁጥጥር ስር ነው” ብለዋል።
በተጨማሪም ኤርሊንግ ሀላንድ ለቀጣዩ ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ያረጋገጡት ፔፕ ጋርዲዮላ “ነገ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ይጀምር አይጀምር የሚለውን ግን በሚቀጥለው ቀን እንወስናለን” ብለዋል።