በጀርመን ቡንደስሊጋ 33ኛ ሳምንት በተካሄዱት ጨዋታዎች ሁለት ክለቦች ወደ ሁለተኛው ዲቪዚዮን ማሽቆልቆላቸው ተረጋግጧል።
ቦሁም ከሜይንዝ ጋር ባደረገው ጨዋታ 4-1 በሆነ ውጤት በመሸነፉ ከቡንደስሊጋው በይፋ ወርዷል።
በተመሳሳይ ዜና ሆልስቴይን ኪየል በፍራይቡርግ 2-1 በሆነ ውጤት በመረታቱ ከቡንደስሊጋው የወረደ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።
በሌላ በኩል ላይፕዚግ ነጥብ በመጣሉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ህልሙ ተጠናቋል።
በተቃራኒው ፍራይቡርግ በሚቀጥለው ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድሉን አጠናክሯል። የመጨረሻውን ጨዋታቸውን ካሸነፉ በቀጥታ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ማለፋቸው እርግጥ ይሆናል።