17.6 C
London
Saturday, June 14, 2025

ሩበን ዲያስ “የሳውዝሀምፕተን ጨዋታ አስቆጥቶኛል፤ የሻምፒየንስ ሊግ ቦታ በእጃችን ነው” ሲል ተናገረ

የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ ሩበን ዲያስ ከሳውዝሀምፕተን ጋር ከተደረገው ጨዋታ በኋላ የሳውዝሀምፕተን የአጨዋወት ስልት እንዳበሳጨው ተናግሯል።

ሩበን ዲያስ በሰጠው አስተያየት “ሳውዝሀምፕተን የተጫወተበት መንገድ በጣም አስቆራኝ ነበር፤ ምንም ነገር ለማድረግ ፍላጎት የነበራቸው አይመስልም” ብሏል።

አክሎም “ስራቸው ሜዳ ላይ ተኝቶ ጨዋታውን ማቋረጥና ጊዜ መግደል ነበር። ጨዋታውን ለማሸነፍ እንኳን ፍላጎት አልነበራቸውም” ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

በመጨረሻም “የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ አሁንም በእጃችን ነው። የምንፈልገውን ለማግኘት እንታገላለን። ሶስት ጨዋታዎች ይቀሩናል፤ ሁሉንም ማሸነፍ እንፈልጋለን” በማለት ለቀጣዮቹ ጨዋታዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here