17.6 C
London
Saturday, June 14, 2025

ራፊንሃ ስለ ኤል ክላሲኮ ዝግጅታቸው ተናገረ

የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጫዋች ራፊንሃ ቡድናቸው ለዛሬው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ራፊንሃ “ኤል ክላሲኮ ሁልጊዜም እንደ ፍጻሜ ጨዋታ ነው” ብሏል። “ይህ ልዩ ዓይነት ጨዋታ ሲሆን መላው ዓለምም ይመለከተዋል” ሲልም አክሏል።

በተጨማሪም ራፊንሃ “በኤል ክላሲኮ ደካማ እና ጠንካራ ቡድን የሚባል ነገር የለም። ሁለታችንም ለላሊጋው ዋንጫ እየተፎካከርን እንገኛለን። ለጨዋታው ዝግጁዎች ነን፤ ጥሩ ውጤትም እናስመዘግባለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብሏል።

ስለ ጨዋታው ያለው ስሜት ሲናገርም “ወደ ኤል ክላሲኮ ስታዲየም በምትገባበት ቅጽበት ውጥረት ይጀምራል። በጨዋታ ወቅት ውጥረቶች የተለመዱ ቢሆኑም በኤል ክላሲኮ ያለው ውጥረት ግን ከወትሮው በላይ ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

በግል ብቃቱ ላይም “ምርጥ አቋሜን ለማሳየት ጠንክሬ እየሰራሁ ነው። በአሁኑ ወቅት ጥሩ እየሰራሁ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ወደፊትም በዚህ መልኩ እንደምቀጥል ተስፋ አለኝ” ሲል ራፊንሃ ተናግሯል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here