የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጫዋች መሐመድ ሳላህ ከቀድሞ የቡድን አጋሩ ሳዲዮ ማኔ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በመጀመሪያው ላይ ጥሩ እንዳልነበር አምኗል።
ሳላህ “ከማኔ ጋር የነበረን ግንኙነት በመጀመሪያው ላይ ያን ያህል የጠነከረ አልነበረም” ብሏል። ሆኖም ግን “እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ እንከባበር ነበር። ይህም በቡድኑ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል ብዬ አላስብም” ሲል ተናግሯል።
ሳላህ አክሎም “ሳዲዮ ማኔ ተፎካካሪ መንፈስ ያለው ሰው እንደሆነ አውቃለሁ። ከሜዳ ውጪ የጠበቀ ግንኙነት ባይኖረንም ሁልጊዜም ግን እንከባበራለን” ብሏል።