17.2 C
London
Saturday, June 14, 2025

አሞሪም “መሸነፍ መፍራት አቁመናል፤ የደረጃ ሰንጠረዡን ሳይ እሸማቀቃለሁ” ሲሉ ተናገሩ

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከዛሬው ሽንፈት በኋላ ክለቡ የትልቅነት አስተሳሰቡን እያጣ መሆኑን በቁጭት ተናገሩ።

አሰልጣኙ “ጨዋታ የመሸነፍ ፍርሃታችን እየቀነሰ መጥቷል” ያሉት አሞሪም “ይህ በትልቅ ክለብ ውስጥ እጅግ አደገኛ ነገር ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ለእኔ ዩሮፓ ሊግን ማሸነፍ ምንም ለውጥ አያመጣም፤ ምክንያቱም ያሉብን ችግሮች ከዚህ እጅግ የላቁ ናቸው። የደረጃ ሰንጠረዡን ሳየው በእውነት እሸማቀቃለሁ” ሲሉ ሩበን አሞሪም ስሜታቸውን ገልጸዋል።

አክለውም “የአንድ ትልቅ ክለብ አስተሳሰብ ከእኛ እየራቀ ነው” ያሉት አሞሪም በዚህ ዓመት ብዙ ለውጦች መደረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም “በቀጣይ ዓመትም ተመሳሳይ የውድድር ዘመን አጀማመር የሚኖረን ከሆነ ቦታዬን ለሌላ ሰው ማስረከብ ይኖርብኛል” በማለት ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here