17.5 C
London
Saturday, June 14, 2025

ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን ሊለቁ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ!

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው በሚፈለገው ደረጃ ካልተቀየረ በቀጣይ የውድድር ዓመት ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቅ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ በሰጡት አስተያየት ቡድኑን በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ማሻሻል ካልቻሉ ማንችስተር ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ መፈለግ እንደሚኖርበት ጠቁመዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዝውውር መስኮቱ ደፋር መሆን እንዳለበት አፅንኦት የሰጡት አሞሪም “በቀጣይ ዓመት እንደዚህ መሆን አንችልም” ብለዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ይህንንም አድርጎ ለውጥ ካልታየ “ቦታውን ለሌሎች ሰዎች አስረክበን መሄድ ይኖርብናል” ሲሉ የወደፊት እጣ ፈንታቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክተዋል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here