የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ትላንት በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃዎች ያሳየው እንቅስቃሴ እጅግ እንዳበሳጫቸው ገለጹ።
አርቴታ “በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ያሳየነው እንቅስቃሴ በፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነበር” ብለዋል። “ሁኔታው በጣም አሳብዶኝ ነበር፤ ይህንን ባላይ እመርጣለሁ” ሲሉም ቁጣቸውን ገለጹ።
ለዚህ ንዴት ብዙ ምክንያቶች እንደነበሩ የጠቆሙት አርቴታ በተለይም የተከላካይ ክፍላቸው የነበረበት ሁኔታ እጅግ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
“በዚህ የውድድር ዓመት ለስድስተኛ ጊዜ በአስር ተጫዋቾች ለመጫወት ተገደናል፤ ግማሽ ያህሉ የቋሚ ቡድናችን ተጫዋቾች ጉዳት ላይ ናቸው፤ ሆኖም ግን ይህ ምንም ለውጥ አያመጣም” ሲሉ አርቴታ ሁኔታውን አስረድተዋል።