17.5 C
London
Saturday, June 14, 2025

የፈረንሳይ ሊግ ወርቅ ጫማ አሸናፊው ኡስማን ዴምቤሌ!

የማርሴው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ዛሬ ምሽት ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች የውድድር ዓመቱን የሊግ ግቦቹን ወደ 21 አሳድጓል። በዚህም ግሪንውድ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ከሆነው የፒኤስጂው ተጫዋች ኡስማን ዴምቤሌ ጋር በግብ ብዛት እኩል መሆን ችሏል።

ይሁን እንጂ የፈረንሳይ ሊግ የወርቅ ጫማ ሽልማትን የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጫዋች ኡስማን ዴምቤሌ ማሸነፉ ተገልጿል። ምክንያቱ ደግሞ ዴምቤሌ ያስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ከመሰን ግሪንውድ ያነሰ በመሆኑ የሊጉን ህግ በመከተል ሽልማቱ ለዴምቤሌ ተሰጥቷል።

በውድድር ዓመቱ ሜሰን ግሪንውድ ሰባት የፍፁም ቅጣት ምት ግቦችን ሲያስቆጥር ኡስማን ዴምቤሌ ግን ያስቆጠረው አንድ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ብቻ ነው።

በተጨማሪም ኡስማን ዴምቤሌ በዚህ የውድድር ዓመት የፈረንሳይ ሊግ ምርጥ ተጫዋች በመባልም መመረጡ ይታወሳል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here