የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ዋንጫዎችን የሚያነሳበት ጊዜ በቅርብ እንደሚሆን ተናግረዋል።
“ዋንጫዎች እየመጡ ነው” ያሉት አርቴታ ደጋፊዎቻቸውን ትንሽ እንዲታገሱ ጠይቀው “የምንችለውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባላችኋለሁ” ብለዋል።
አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለምን እንዳጣ ተጠይቀው ሲመልሱ “ቀይ ካርድ ነው” ብለዋል። አክለውም “ሌላው ዋንጫ ያጣንበት ምክንያት ጉዳቶች ነበሩ፣ ነገር ግን ለዋንጫው በጣም ተቃርበን ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።