17.5 C
London
Saturday, June 14, 2025

ብሩኖ ጉማሬሽ “ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ እንችላለን” አለ

የኒውካስል ዩናይትድ አማካይ ተጫዋች ብሩኖ ጉማሬሽ ቡድናቸው የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት አቅም እንዳለው ተናግሯል።

“መቼ እንደሆነ በትክክል አላውቅም፣ ነገር ግን ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ እንደምንችል በእርግጠኝነት አምናለሁ” ሲል ጉማሬሽ አስተያየቱን ሰጥቷል።

“አንድ ዋንጫ ብቻ በቂ አይደለም” ያለው ብራዚላዊው አማካይ በቀጣይነትም ቡድኑ ብዙ ዋንጫዎችን የማንሳት አቅም እንዳለው ገልጿል።

በተጨማሪም “ሶስት ወይም አራት ተጫዋቾችን በአዲስ መልክ ካስፈረምን ክለቡ በትልቁ ደረጃ ተፎካካሪ መሆን ይችላል” ሲል ተናግሯል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here