17.5 C
London
Saturday, June 14, 2025

አርኔ ስሎት በታዋቂው የአንፊልድ ባነር ሊካተት ነው!

በአንፊልድ ስታዲየም ከሚታዩት ዝነኛ ባነሮች አንዱ የሊቨርፑልን ታሪካዊ አሰልጣኞች ምስል የያዘው ነው። ይህ ባነር እንደ ቢል ሻንክሊ፣ ቦብ ፓይስሌይ፣ ጆ ፋጋን፣ ኬኒ ዳግሊሽ፣ ራፋኤል ቤኒቴዝ እና ዩርገን ክሎፕ ያሉ የቀድሞ የክለቡን ድንቅ አሰልጣኞች ያካትታል።

ይህ የአንፊልድ መለያ ምልክት የሆነው ባነር ሊቨርፑል በሜዳው በሚጫወትባቸው ጨዋታዎች ላይ ሁልጊዜ ይታያል። አሁን ደግሞ አዲሱ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በክለቡ የመጀመሪያ አመት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማሸነፍ በሚቀጥለው አመት በዚህ ታዋቂ ባነር ላይ ሊካተት እንደሚችል ተገልጿል።

አሰልጣኞች በታዋቂው ባነር የሚካተቱት ምን ሲሰሩ ነው?

የባነሩ ባለቤት የሆኑ የሊቨርፑል ደጋፊዎች እንደገለጹት፣ በታዋቂው ባነር ላይ ለመካተት ሊቨርፑልን በኃላፊነት የመሩ አሰልጣኞች የተወሰኑ ስኬቶችን ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ አሰልጣኞች በምስሉ ላይ ለመካተት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወይም በአውሮፓ መድረክ ላይ ዋንጫ ለሊቨርፑል ማምጣት አለባቸው።

ይህንን ታሪካዊ ባነር የፈጠረው እና ባለቤት የሆነው ከሃያ ሁለት አመታት በፊት የተመሰረተው በአየርላንድ ዱብሊን የሚገኘው የሊቨርፑል ደጋፊዎች ቡድን ነው።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here