የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለቀድሞ የቡድን አጋሩ ስኮት ማክቶሚናይ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፏል።
ፈርናንዴዝ “እንኳን ደስ አለህ ጓደኛዬ! ሁልጊዜም ጠንካራ፣ ሥነ ምግባር ያለው እና ቆራጥ ነበርክ” ሲል ማክቶሚናይን አሞካሽቷል። አክሎም “አሁን ካለህ በራስ መተማመን ጋር ያለህ አቅም ከምንጊዜውም በበለጠ ደምቆ ታይቷል፤ አሁን ያንተ ጊዜ ነው፣ ተደሰትበት” ብሏል።
ማክቶሚናይ በናፖሊ ቤት የሴሪአውን ስኩዴቶ ማሳካቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሊጉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል መመረጡም አይዘነጋም።