የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አዲስ የውድድር ዘመን ለመጀመር ቀድመው ነገሮችን ማየታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
ዩናይትድን መረከባቸው ይፀፀታቸው እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ሩበን አሞሪም “በአሁኑ ሰዓት ከአዲሱ የውድድር ዘመን በፊት ስድስት ወራት ቀድሜ በመምጣቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።
“በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ሊፈጠሩ ይችሉ የነበሩ በርካታ ችግሮችን አውቀንበታል” ሲሉ የገለፁት ሩበን አሞሪም፣ ሊገጥሙን የነበሩ በርካታ ስቃዮችን አስቀርተናል ሲሉ ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን በክረምት ለመረከብ ፈልገው በክለቡ ግፊት በአመቱ አጋማሽ ወደ ኦልድትራፎርድ መድረሳቸው አይዘነጋም።
አሰልጣኙ አክለውም ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስ አመቱን በጥሩ ሁኔታ መጨረስ አለብን በማለት ተናግረዋል።