21.5 C
London
Friday, June 13, 2025

ኢንተር ሚላን ለሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ከፍተኛ የትኬት ጥያቄ ቀረበለት!

የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለመመልከት ከደጋፊዎቹ ከፍተኛ የትኬት ጥያቄ እንደቀረበለት ተዘግቧል። ከ80,000 በላይ የሚሆኑ የኢንተር ሚላን ደጋፊዎች ጨዋታውን ለመታደም የትኬት ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል።

ይህ የቀረበው የትኬት ጥያቄ ከሁለት ዓመት በፊት በኢስታንቡል የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ከቀረበው ጥያቄ ብዛት እንደሚበልጥ ተገልጿል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) ለእያንዳንዱ ክለብ 18,000 ትኬቶችን የሚሰጥ ሲሆን፣ ኢንተር ሚላን ለታማኝ ደጋፊዎቹ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ በጀርመን ሙኒክ፣ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም ይካሄዳል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here