የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ጋሪ ኔቪል አርሰናል ቀጣዩን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እንደሚያሸንፍ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ኔቪል፣ “ቀጣይ ዓመት በድጋሚ አርሰናልን እደግፋለሁ” በማለት፣ የሰሜን ለንደን ክለብ ሊጉን የማሸነፍ አቅም እንዳለው ተናግሯል። አርሰናል ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ሁለቴ ሁለተኛ ደረጃን ማጠናቀቁን የጠቀሰው ኔቪል፣ “ቀጣይ ይሳካላቸዋል” ሲል ያላቸውን እምነት ገልጿል።