በአዲስ የውድድር ቅርፅ ነገ በሚጀመረው የፊፋ የክለቦች የዓለም ዋንጫ የመግቢያ ቲኬቶች ላይ ቅናሽ መደረጉ ተዘግቧል። የዋጋ ቅናሹ “በፍላጎት ማነስ” ምክንያት የተደረገ ሲሆን፣ የቲኬት ዋጋ እስከ 300 ዶላር የነበረው አሁን ወደ 48 ዶላር ዝቅ ብሏል።
የውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታ በሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ማያሚ እና በግብፁ አል አህሊ መካከል ሲደረግ፣ ለዚህ ጨዋታ የመግቢያ ዋጋው እስከ 250 ዶላር መውረዱ ታውቋል።