የማንችስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የክለቦች ዓለም ዋንጫን “አስፈላጊ ውድድር” ሲሉ ገልጸውታል። አሰልጣኙ አክለውም “አጠቃላይ የአለም ህዝብ ይመለከተናል” በማለት የውድድሩን ፋይዳ አብራርተዋል።
ጋርዲዮላ አብዛኞቹ የአለም ምርጥ ክለቦች የሚሳተፉበት ውድድር መሆኑን አውስተው፣ በውድድሩ ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት ሲገልጹ “የማረጋግጥላችሁ ነገር ወደ አሜሪካ የምንሄደው ውድድሩን ለማሸነፍ ነው” ብለዋል።