የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የባየር ሌቨርኩሰኑን አማካይ ፍሎረን ዊርትዝን በ136.3 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ዋጋ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። ከዚህ ውስጥ 117.5 ሚሊዮን ዩሮ ቅድመ ክፍያ ሲሆን፣ ቀሪው 18.8 ሚሊዮን ዩሮ በቀጣይ የሚከፈል ይሆናል።
ሊቨርፑል ተጫዋቹን በአንፊልድ ለአምስት ዓመታት ለማቆየት ተስማምቷል። ዊርትዝ በቡንደስሊጋው ባየር ሙኒክ በጥብቅ ይፈለግ የነበረ ቢሆንም፣ ተጫዋቹ ከወራት በፊት ሊቨርፑልን እንደመረጠ ማሳወቁ ይታወቃል።