ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ማቲየስ ኩኛ ማንቸስተር ዩናይትድ ለእሱ ልዩ ክለብ እንደሆነ ገልጿል። “ለእኔ የትኛውም ክለብ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር አይወዳደርም” በማለት ኩኛ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ኩኛ አክሎም “ውሳኔዬ ክለቡ ለእኔ ምን ማለት እንደሆነ እና ስኬታማ እንደምንሆን ያለኝን እምነት ያሳያል” ብሏል። ተጫዋቹ “ማንቸስተር ዩናይትድን ከሁሉም በላይ ማስቀመጥ እፈልጋለሁ” በማለት ለቀያይ ሰይጣኖቹ ያለውን ተመላኪነት አሳይቷል።